ዘፍጥረት 30:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያ ዳግመኛ ፀነሰችና ለያዕቆብ ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም ደግማ ፀነስች፤ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች |
እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው።