ዘፍጥረት 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሸ ጊዜ፥ እግዚአብሔር አምላክ በአትክልቱ ቦታ ውስጥ ሲመላለስ ድምፁን ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱ እግዚአብሔር አምላክ እንዳያያቸው በዛፎች መካከል ተደበቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ እግዚአብሔር አምላክ በአትክልቱ ስፍራ ሲመላለስ አዳምና ሚስቱ ድምፁን ሰምተው ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በዛፎቹ መካከል ተሸሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ በገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱ ከእግዚእብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። |
የእስራኤል ሕዝብ አዌን በተባለ ከተማ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት የሚሠሩባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ በመሠዊያዎቻቸውም ላይ እሾኽና አሜከላ ይበቅሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ተራራዎችን “ደብቁን!” ኮረብቶችንም “ጋርዱን!” ይላሉ።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።
ይህም ሁኔታቸው ሕግ የሚያዘው ነገር ሁሉ በልባቸው የተጻፈ መሆኑን ያሳያል፤ ደግሞም ኅሊናቸው ይመሰክርባቸዋል፤ ኅሊናቸው አንዳንዴ ይወቅሳቸዋል፤ አንዳንዴም ይደግፋቸዋል።
ሰፈራችሁን በሕጉ መሠረት በንጽሕና ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሊጠብቃችሁና በጠላቶቻችሁም ላይ ድልን ሊያጐናጽፋችሁ በሰፈራችሁ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ፊቱን ከእናንተ እንዲመልስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ነገር ሁሉ አታድርጉ።
ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።