አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።
ዘፍጥረት 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር እሾኽና አሜከላ ታበቅላለች፤ አንተም የዱር ተክሎችን ትበላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርም እሾኽና አሜከላ ታበቅልብሃለች፤ ከቡቃያዋም ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፥ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። |
አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።
“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
የእሾኽ ቊጥቋጦና ኲርንችት በሕዝቤ ምድር ላይ በቅሎአል፤ ሕዝቦች በደስታ ይኖሩባቸው ስለ ነበሩት ቤቶችና በደስታ ተሞልታ ስለ ነበረችው ስለዚህች ከተማ አልቅሱ!
ከዚያን በኋላ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ ስለዚህም አራሙቻ እንዲበቅልበት፥ በኲርንቺትና በእሾኽ እንዲሸፈን አደርጋለሁ፤ ዝናብም እንዳያዘንብበት ደመናን አዛለሁ።”
አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።