በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ “ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረምን? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?” አለው።
ዘፍጥረት 29:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “ታላቂቱ ሳትዳር፥ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም እንዲህ አለው፤ “በአገራችን ታላቋ እያለች ታናሿን መዳር የተለመደ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም እንዲህ አለ፦ “በአገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንስጥ ዘንድ ወግ አይደለም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም እንዲህ አለ፥ “በሀገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንሰጥ ዘንድ ወግ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም እንዲህም አለ፦ በአገራችን ታላቂቱ ሳለች ታናሺቱን እንስጥ ዘንድ ወግ አይደለም፤ |
በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ “ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረምን? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?” አለው።