ዘፍጥረት 29:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያኽል ደመወዝ ላስብልህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባ ያዕቆብን፣ “ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ልታገለግለን አይገባምና ደመወዝህ ምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ያዕቆብን፦ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ደመወዝህ ምንድነው? ንገረኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን፥ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ አታገለግለኝም ደመወዝህ ምንድን ነው? ንገረኝ” አለው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ያዕቆብን፦ ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ምንዳህ ምንድር ነው? ንገረኝ አለው። |
ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።
የእናቱም ዘመዶች እርሱን ወክለው ይህንኑ ለሴኬም ሰዎች ነገሩአቸው፤ የሴኬም ሰዎችም እርሱ ወንድማችን ነው ብለው አቤሜሌክን የመከተል ፍላጎት አደረባቸው።