La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 28:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ከዚህ በፊት ካገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም ወደ እስማኤል ሄደ፣ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን፣ የነባዮትን እኅት ማዕሌትን በሚስቶቹ ላይ ተጨማሪ አድርጎ አገባ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ፥ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶቹ ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ፥ እርሷም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዔሳው ወደ ይስ​ማ​ኤል ሄደ፤ ቤሴ​ሞ​ት​ንም በፊት ካሉ ሚስ​ቶቹ ጋር ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ወሰ​ዳት፤ እር​ስ​ዋም የና​ኮር ወን​ድም የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የሆ​ነው የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅና የና​ቡ​ዓት እኅት ናት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዔሳው ወደ እስማኤል ሄደ ማዕሌትንም በፊት ካሉት ሚስቶች ጋር ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ እርስዋም የአብርሃም ልጅ የሆነ የእስማኤል ልጅና የነባዮት እኅት ናት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 28:9
6 Referencias Cruzadas  

ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆነው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ።


የረዑኤል ልጆች፦ ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና ሚዛ ናቸው፤ እነዚህም ዔሳው ባሴማት ከምትባለው ሚስቱ የወለዳቸው የልጅ ልጆች ናቸው።


ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተወለዱት የነገድ አለቆች፦ የዑሽ፥ ያዕላምና ቆሬ ናቸው፤ እነዚህ ከዐና ልጅ ከኦሆሊባማ የተወለዱ የዔሳው ትውልድ የነገድ አለቆች ናቸው።


ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የሒታዊው የኤሎን ልጅ ዓዳ፥ የሒዋዊው የጺባዖን ልጅ ዐና የወለዳት ኦሆሊባማን እና፥


የነባዮት እኅት የነበረችው የእስማኤል ልጅ ባሴማት ናቸው።