La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 27:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይስሐቅም “ልጄ በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅሃለሁ” አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም፣ “በል እንግዲህ ልጄ፤ እንድመርቅህ፣ ዐድነህ ካመጣኸው አቅርብልኝና ልብላ” አለው። ያዕቆብም ምግቡን ለአባቱ አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም አመጣለት፤ እርሱም በላ፤ ጠጣም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም፦ “ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ” አለ። አቀረበለትም፥ በላም፥ የወይን ጠጅ አመጣለት፥ እርሱም ጠጣ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ፥ ከአ​ደ​ን​ኸው እን​ድ​በ​ላና ነፍሴ እን​ድ​ት​ባ​ር​ክህ አም​ጣ​ልኝ” አለው። አቀ​ረ​በ​ለ​ትም፤ በላም፤ ወይ​ንም አመ​ጣ​ለት፤ እር​ሱም ጠጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ አለ። አቀረበለትም፥ በላም የወይን ጠጅ አመጣለት እርሱም ጠጣ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 27:25
3 Referencias Cruzadas  

“በእርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም “አዎ፥ ነኝ” አለ።


ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ “ልጄ ሆይ፥ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው፤


ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሠርተህ አምጣልኝ፤ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።”