ዘፍጥረት 27:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ወደ አባቱ ሄደና “አባባ!” አለው፤ እርሱም “እነሆ፥ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ወደ አባቱ ሄዶ፣ “አባቴ ሆይ” አለ፤ ይሥሐቅም፣ “እነሆ፤ አለሁ ልጄ፤ ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አባቱም ገብቶ፦ “አባቴ ሆይ” አለው እርሱም፦ “እነሆኝ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አባቱም አግብቶ፥ “አባቴ ሆይ፥” አለው፦ እርሱም፥ “እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አባቱም ገብቶ፦ አባቴ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ አንተ ማን ነህ? አለ። |
ያዕቆብም “የበኲር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ፥ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ” አለው።
እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥