La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 26:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቤሜሌክም “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤ እኛንም ኃጢአተኞች ልታደርገን ነበር፤”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቢሜሌክም መልሶ፣ “እንዲህ ያለ ነገር ያደረግህብን ለምንድን ነው? ከሰዎቻችን አንዱ ሚስትህን ቢደፍራት ኖሮ በእኛ ላይ በደል አስከትለህብን ነበር እኮ!” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቢሜሌክም አለ፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቢሜልውክም አለ፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ከሕዝብ አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀረው ነበር፥ ኃጢአትንም ልታመጣብን ነበር።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 26:10
4 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ አቤሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ “ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ ‘እኅቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኛል ብዬ ስለ ፈራሁ ነው” ብሎ መለሰ።


በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ “ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረምን? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?” አለው።