የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዐሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።
ዘፍጥረት 24:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጒልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈጽም በመሐላ ቃል ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም አገልጋዩ እጁን ከጌታው ከአብርሃም ጭን በታች አድርጎ ስለዚህ ጕዳይ ማለለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሌውም ከጌታው ከአብርሃም ጭን በታች እጁን አደረገ ስለዚሁም ነገር ማለለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውም በጌታው በአብርሃም እጅ ላይ እጁን አደረገ፤ ስለዚሁም ነገር ማለለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውም ከጌታው ለአብርሃም ጭን በታች እጁን አደረገ ስለዚህም ነገር ማለለት። |
የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዐሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።