ዘፍጥረት 24:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ “ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያኽል ከእኛ ጋር ትቈይ፤ ከዚያ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሟና እናቷም፣ “ልጅቷ ከእኛ ጋራ ቢያንስ ዐሥር ቀን ያህል ትቈይና ከዚያ በኋላ ልትሄድ ትችላለች።” ብለው መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምዋና እናትዋም፦ “ብላቴናይቱ አንድ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ ከእኛ ዘንድ ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለች” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷ እናቷና ወንድምዋ፦ “ብላቴናዪቱ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ በእኛ ዘንድ ትቀመጥ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳለች” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምዋና እናትዋም፦ ብላቴናይቱ አንድ አሥር ቀን ያህል እንኳ ከእኛ ዘንድ ትቀመጥ ከዚያም በኍላ ትሄዳለች አሉ። |
ከጥቂት ቀኖች በኋላ እርስዋን ለማግባት ወደዚያ ተመልሶ ሄደ፤ በጒዞም ላይ ሳሉ ያንን የገደለውን አንበሳ ሁኔታ ለማየት ከመንገድ ዞር አለ፤ በድኑን ንቦች ሰፍረውበት በውስጡም ማር. መኖሩን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ተደነቀ፤