ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው።
ዘፍጥረት 22:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይሥሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም ዐብረው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም የመሥዋዕቱን ዕንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ። |
ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው።
ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፥ “እነሆ! አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ! ከቶ ከአንተ አልለይም!” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ጒዞአቸውን ቀጠሉ።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።