Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህ በኋላ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ ከአህያው ጋር እዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ከሰገድን በኋላ እንመለሳለን” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አገልጋዮቹንም “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቈዩን፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ ሄደን ለእግዚአብሔር ሰግደን እንመለሳለን” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከዚህ በኋላ አብርሃምም አገልጋዮቹን፥ “አህያውን ይዛችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ተራራ ሄደን እንሰግዳለን፤ ሰግደንም ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው፦ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 22:5
6 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ከሞት የማስነሣት ችሎታ እንዳለው አብርሃም በማመኑ ልክ ከሞት እንደ ተነሣ ያኽል ይስሐቅን እንደገና አገኘው።


እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ።


በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ።


አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥


ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።


ሙሴም ለመሪዎቹ “እንደገና ወደ እናንተ ተመልሰን እስክንመጣ በዚህ ቈዩን፤ አሮንና ሑርም እነሆ፥ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ስለዚህም በመካከላችሁ ጥልና ክርክር ያለበት ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios