ዘፍጥረት 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክ “ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት ጓደኛ እፈጥርለታለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚእብሔርም፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ የምትሆነውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚእብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረት እንፍጠርለት። |
አንድ ሰው እጮኛውን ላለማግባት ከወሰነ በኋላ ይህን ማድረጉ ለልጅትዋ መልካም ያላደረገ መሆኑ ቢሰማው፥ ከዚህም ሌላ እርስዋን ለማግባት ያለው ፍላጎት ጠንካራ ቢሆንና መጋባታቸውም ትክክል ከመሰለው እንደ ተመኘው ቢያገባት ኃጢአት አይሆንበትም፤ ስለዚህም ይጋቡ።
እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም።