ዘፍጥረት 19:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው “ወዳጆቼ ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አለ፤ “ወዳጆቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንዲህ ያለውን ክፉ ነገር አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ለእናንተ አግባባችሁ አይደለም፤ በእነዚህ ላይ ክፉ አታድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ |
እነሆ፥ ሁለት ያላገቡ ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ወደ እናንተ ላምጣላችሁና በእነርሱ ላይ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ በእነዚህ ሰዎች ግን ምንም ነገር አታድርጉ፤ እነርሱ የእኔ እንግዶች ስለ ሆኑ ልጠነቀቅላቸው ይገባኛል።”
እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።
ስለዚህ እርስ በርሳቸው በገዛ አካላቸው ላይ አሳፋሪ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ርኲሰት ለሞላበት ለክፉ ምኞታቸው ተገዢዎች እንዲሆኑ ተዋቸው።
በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።
ሽማግሌው ግን ወደ ውጪ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “አይሆንም ወዳጆቼ ሆይ! እባካችሁ ይህን የመሰለ አስከፊ ነገር አታድርጉ! ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው፤