ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
ዘፍጥረት 19:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ሁኔታ ሁለቱም የሎጥ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሁለቱም የሎጥ ሴት ልጆች ከአባታቸው አረገዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። |
ስለዚህ በዚያን ምሽት አባታቸውን እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታናሽቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች፤ አሁንም እጅግ ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
እነሆ፥ ሁለት ያላገቡ ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ወደ እናንተ ላምጣላችሁና በእነርሱ ላይ የፈለጋችሁትን ነገር አድርጉ፤ በእነዚህ ሰዎች ግን ምንም ነገር አታድርጉ፤ እነርሱ የእኔ እንግዶች ስለ ሆኑ ልጠነቀቅላቸው ይገባኛል።”
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ ‘የሎጥ ዘሮች የሆኑትን ሞአባውያንን አታስቸግሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ የዔርን ከተማ ለእነርሱ መኖሪያ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህም ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁም።’ ”
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።
በዚህም ጊዜ ሳሙኤል “የአንተ ሰይፍ ብዙዎች እናቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ የአንተም እናት ልጅ አልባ ሆና ትቀራለች” አለው። ከዚህም በኋላ በጌልገላ በሚገኘው በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት አጋግን ቈራርጦ ጣለው።