ዘፍጥረት 18:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ፤ እንደገና ልናገር፤ ምናልባት ሠላሳ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ሠላሳ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?” እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ። |
አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ አሁንም እንደገና በመናገሬ ይቅር በለኝ፤ ምናልባት ኻያ ቢገኙስ?” አለ፤ እግዚአብሔርም “ኻያ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ።
“ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
ቀጥሎም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ እንደገና አንድ ጊዜ እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ይኸውም በበግ ጠጒሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ምልክት እንዲታይ ልጠይቅ፤ በዚህን ጊዜ የጠጒሩ ባዘቶ ደረቅ ሆኖ በዙሪያው ያለው ምድር እርጥብ እንዲሆን አድርግልኝ።”