አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
ዘፍጥረት 17:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ሸለፈታቸውን ገረዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔ እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። |
አብራም የወንድሙ ልጅ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ ተወልደው የጦር ልምምድ ያላቸውን 318 ሰዎች በትጥቅ አደራጅቶ አራቱን ነገሥታት በመከታተል እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
እንደገናም እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ከትውልድ እስከ ትውልድ ጠብቁ፤
ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው።