አብራምም እነዚህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አምጥቶ እያንዳንዱን እየቈረጠ በሁለት ከፈለው፤ የተከፈሉትንም ትይዩ አድርጎ በሁለት መስመር አስቀመጣቸው። ወፎቹን ግን ቈርጦ አልከፈላቸውም።
ዘፍጥረት 15:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞራዎች የተቈራረጠውን ሥጋ ለመብላት ሲመጡ አብራም አባረራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞሮችም ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራም ግን አባረራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞራዎችም በተቈረጠው ሥጋቸው ላይ ወረዱ፤ አብራምም በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ አባረራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው። |
አብራምም እነዚህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አምጥቶ እያንዳንዱን እየቈረጠ በሁለት ከፈለው፤ የተከፈሉትንም ትይዩ አድርጎ በሁለት መስመር አስቀመጣቸው። ወፎቹን ግን ቈርጦ አልከፈላቸውም።
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእነርሱ የምለውን ያውቁ ዘንድ ይህን ንገራቸው፤ የተዋቡ ላባዎችና ታላላቅ ክንፎች ያሉት አንድ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ ይህም ንስር ወደ ሊባኖስ ተራራዎች በረረ፤ በአንድ የሊባኖስ ዛፍ ላይ አርፎም ጫፉን በመቊረጥ የንግድ ሥራ ወደ ተስፋፋበት ወደ አንድ አገር አምጥቶም ነጋዴዎች በበዙባት ከተማ አኖረው።
“እንዲሁም ታላላቅ ክንፎችና ብዙ ላባዎች ያሉት ሌላ ግዙፍ ንስር ነበረ፤ አሁን እንግዲህ የወይን ተክሉ ሥሮቹንና ቅርንጫፎቹን ወደ ንስሩ ዘረጋ፤ ይህንንም ያደረገው ከተተከለበት መደብ ውሃ ያጠጣው ዘንድ ነው።