አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥
ዘፍጥረት 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰዶምም ንጉሥ አብራምን “በምርኮ ያገኘኸውን ሀብት ሁሉ ለራስህ ውሰድ፤ ሰዎቼን ግን መልስልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰዶም ንጉሥም አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰዶም ንጉሥም አብራምን፦ ሰዎቹን ስጠኝ፥ ከብቱን ግን ለአንተ ውሰድ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዶም ንጉሥም አብራምን፥ “ሰዎቹን ስጠኝ፤ ፈረሶቹን ግን ለአንተ ውሰድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰዶም ንጉሥም አብራምን፤ ሰዎቹን ስጠኝ፥ ከብቱን ግን ለአንተ ውሰድ አለው። |
አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥
በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጒድጓዶች ነበሩ፤ ስለዚህ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ከጦርነቱ ሸሽተው ለማምለጥ በሞከሩ ጊዜ በጒድጓዶቹ ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩት ሦስት ነገሥታት ግን ወደ ተራራዎቹ ሸሹ።
በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።”