እርስ በርሳቸውም “ኑ! ጡብ እንሥራ፤ እንዲጠነክርም በእሳት እንተኲሰው” ተባባሉ፤ በዚህ ዐይነት የሚገነቡትን ጡብ አገኙ፤ በአንድነት የሚያጣብቁበትንም ቅጥራን አገኙ።
ዘፍጥረት 14:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጒድጓዶች ነበሩ፤ ስለዚህ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ከጦርነቱ ሸሽተው ለማምለጥ በሞከሩ ጊዜ በጒድጓዶቹ ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩት ሦስት ነገሥታት ግን ወደ ተራራዎቹ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጕድጓዶች ስለ ነበሩ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጕድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራሮች ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሲዲም ሸለቆ ግን የዝፍት ጉድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥ የገሞራ ንጉሥም ሸሹና ወደዚያ ወደቁ፥ የቀሩትም ወደ ተራራ። ሸሹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሲዲም ሸለቆ ግን የዝፍር ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥ የገሞራ ንጉሥም ሸሹ። |
እርስ በርሳቸውም “ኑ! ጡብ እንሥራ፤ እንዲጠነክርም በእሳት እንተኲሰው” ተባባሉ፤ በዚህ ዐይነት የሚገነቡትን ጡብ አገኙ፤ በአንድነት የሚያጣብቁበትንም ቅጥራን አገኙ።
አብራም ከዶርላዖሜርና ከእነርሱ ጋር አብረው የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፥ የሰዶም ንጉሥ “የንጉሥ ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው በሻዌህ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ፤
የተዋጉትም ከዔላም፥ ከጎይም፥ ከባቢሎንና ከኤላሳር ነገሥታት ጋር ነበር፤ አምስቱ ነገሥታት ከአራቱ ነገሥታት ጋር የተዋጉት በዚህ ዐይነት ነበር።
ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
ከአሸባሪ ድምፅ የሚሸሽ በተቈፈረ ጒድጓድ ውስጥ ይወድቃል፤ ከጒድጓድ ዘሎ ለማምለጥ የሚሞክርም በወጥመድ ይያዛል፤ ከሰማይ ብርቱ ዝናብ ይዘንባል፤ የምድር መሠረቶችም ይናወጣሉ።
“ከሽብር የሚያመልጠው፥ ጒድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጒድጓድ ዘሎ የሚወጣውም ሁሉ በወጥመድ ይያዛል፤ ሞአብን የምቀጣበትን ቀን አመጣባታለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
እስራኤላውያን በሜዳና በምድረ በዳ ቀደም ሲል የዐይ ወታደሮች እነርሱን አሳደዋቸው በነበረው ስፍራ ሁሉንም ገድለው ከጨረሱ በኋላ ወደ ዐይ ከተማ ገብተው በዚያ የተረፉትንም በሰይፍ ፈጁአቸው።