በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
ዘፍጥረት 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ሦስተኛ ቀን ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ። ሦስተኛም ቀን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን። |
በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤