ገላትያ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓላማው ጥሩ ከሆነ መትጋት ምንጊዜም መልካም ነው፤ ነገር ግን ይህ መትጋታችሁ እኔ ከእናንተ ጋር በምኖርበት ጊዜ ብቻ አይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ መልካም ለሆነ ነገር ሁሉ ብትቀኑ መልካም ነው፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ጋር ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅናትስ ዘወትር ለመልካም ሥራ ልትቀኑ ይገባል፤ ነገር ግን እኔ ከእናንተ ዘንድ ባለሁበት ጊዜ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው። |
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
ሌሎች ሰዎች ስለ እናንተ በመጨነቅ ያስባሉ፤ ይሁን እንጂ ይህን የሚያደርጉት ለመልካም አይደለም፤ የእነርሱ ፍላጎት እናንተ ከእኛ እንድትለዩና ለእነርሱ በትጋት እንድታስቡ ነው።
ከበፊቱ የተለየ ሁኔታ እንዳሳያችሁ አሁን ከእናንተ ጋር መሆን በፈለግሁ ነበር፤ ነገር ግን ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለማወቄ ግራ ገብቶኝ ተጨንቄአለሁ።
እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ የክርስቶስን ወንጌል የሚያስመሰግን ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁም ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ወንጌልን በኅብረት ለማዳረስ መጋደላችሁን እሰማለሁ።
ወዳጆቼ ሆይ! እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁልጊዜ ታዛዦች እንደ ነበራችሁ፥ ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ፤ ስለዚህ እያንዳንዳችሁ መዳናችሁን ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮት ተግታችሁ ሥሩ።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።