ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።”
ዕዝራ 7:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከኤፍራጥስ ምዕራብ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ በሰማይ አምላክ ሕግ ምሁር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ ትሰጡት ዘንድ አዝዣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤፍራጥስ ማዶ የምትገኙ በጅሮንዶች ሁሉ፣ የሰማይ አምላክ ሕግ መምህር የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት እኔ ንጉሥ አርጤክስስ እነሆ አዝዣለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ንጉሡ አርተሰስታ በወንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ሁሉ አዘጋጁለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ላሉት በጅሮንዶች ሁሉ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ ‘የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ሁሉ አዘጋጁለት፤ |
ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።”
ይህም ሁሉ ሆኖ፥ ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ያሉትን አገሮች ሁሉ በማስገበር ቀረጥና ግብር የሚያስከፍሉ ኀያላን ነገሥታት ነግሠውባት ነበር።
ከዚህ በኋላ ዳርዮስ የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ ለሆንከው ለታተናይ፥ ለሸታርቦዝናይና በኤፍራጥስ ምዕራብ ለሚገኙ ተባባሪዎቻችሁ ሁሉ፦ ከቤተ መቅደሱ ራቁ፤
ከብዙ ጊዜ በኋላ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን፥ ዕዝራ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በዚያ ይኖር ነበር፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች የትውልድ ሐረግ እስከ ታላቁ ሊቀ ካህናት አሮን ድረስ ሲቈጠር እንደሚከተለው ነው፦ ዕዝራ የሠራያ ልጅ ሲሆን፥ ሠራያ የዐዛርያ ልጅ፥ ዐዛርያ የሒልቂያ ልጅ፥ ሒልቂያ የሻሉም ልጅ፥
እስከ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብር፥ እስከ ዐሥር ሺህ ኪሎ ስንዴ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይን ጠጅ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይራ ዘይትና የሚያስፈልገውንም ያኽል ጨው ስጡት።
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ ሊቅ ነበር፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
ንጉሠ ነገሥቱ የሰጣቸውንም ሰነድ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ላሉት ገዢዎችና ባለሥልጣኖች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ በማገዝ ድጋፋቸውን ሰጡ።
ከዚያም በመቀጠል ወደ ይሁዳ ማለፍ እንዲፈቅዱልኝ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ክፍለ ሀገር ላሉት አገረ ገዢዎች የይለፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ለንጉሠ ነገሥቱ ልመና አቀረብኩ፤
በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤