ይህም ሁሉ ሆኖ፥ ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ያሉትን አገሮች ሁሉ በማስገበር ቀረጥና ግብር የሚያስከፍሉ ኀያላን ነገሥታት ነግሠውባት ነበር።
ዕዝራ 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኔ ሌላ ትእዛዝ እስካስተላልፍ ድረስ እነዚያ ሰዎች ከተማይቱን እንደገና መሥራታቸውን ያቆሙ ዘንድ እዘዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እኔ ትእዛዝ እስከምሰጥበት ድረስ ይህች ከተማ እንደ ገና እንዳትሠራ ሥራውን ያቆሙ ዘንድ ለእነዚህ ሰዎች ትእዛዝ አስተላልፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲተዉ፥ እኔም ትእዛዝ እስከምሰጥ ድረስ ይህች ከተማ እንዳትሠራ ትእዛዝ ስጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲተዉ፥ ይህችም ከተማ እንዳትሠራ ትእዛዝ ስጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲተዉ፥ እኔም እስካዝዝ ድረስ ይህች ከተማ እንዳትሠራ ትእዛዝ ስጡ። |
ይህም ሁሉ ሆኖ፥ ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ያሉትን አገሮች ሁሉ በማስገበር ቀረጥና ግብር የሚያስከፍሉ ኀያላን ነገሥታት ነግሠውባት ነበር።