ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።”
ዕዝራ 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሠ ነገሥቱም ለዚህ ደብዳቤ ከዚህ የሚከተለውን መልስ ላከ፦ “ለአገረ ገዢው ረሑም፥ ለአውራጃ ጸሐፊው ሺምሻይ፥ እንዲሁም በሰማርያና ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ለሚኖሩ ተባባሪዎችህ ሁሉ፥ ሰላም ለእናንተ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ይህን መልስ ላከ፤ ለአገረ ገዥው ሬሁም፣ ለጸሓፊው ሲምሳይ፣ በሰማርያና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚኖሩ ተባባሪዎቻቸው፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፦ “ለአዛዡ ለሬሑምና ለጸሐፊውም ለሺምሻይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶ ባለ አገር ለተቀመጡ ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው ሰላም! አሁንም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሓፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡትና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ለአዛዡ ለሬሁም፥ ለጸሐፊውም ለሲምሳይ፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶም ለተቀመጡት እና ለቀሩት ተባባሪዎቻቸው እንዲህ የሚለውን መልስ ላከ፤ |
ከዚህም የተነሣ፥ ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ ግርማዊነትዎ ከኤፍራጥስ ማዶ በሚገኙት ክፍላተ ሀገሮች ላይ ምንም ይዞታ እንደማይኖርዎ እንገልጻለን።”
አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በተነሣበትም ዘመን፥ እንደገና ቢሽላም፥ ሚትረዳት፥ ጣብኤልና ሌሎቹ የእነርሱ ግብረ አበሮች የክስ ደብዳቤ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ጻፉባቸው፤ ይህም ደብዳቤ የተጻፈው በሶርያ ፊደልና ቋንቋ ሲሆን ተተርጒሞ በንባብ እንዲሰማ የተላከ ነበር።
“ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፥ የሰማይ አምላክ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ረገድ ታላቅ ምሁር ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፦ ሰላም ላንተ ይሁን፤
ንጉሡ ናቡከደነፆር በዓለም ሁሉ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ በየአገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች በጽሑፍ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ስለዚህ በሮም ለምትኖሩ፥ እግዚአብሔር ለወደዳችሁና ወገኖቹ እንድትሆኑ ለጠራችሁ ሁሉ፦ ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።