ዘፀአት 8:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴ እንዳለው ሁሉ አደረገ፤ የዝንብ መንጋውም ከንጉሡና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ሁሉ ፊት አንድ ሳይቀር ተወገደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴ የለመነውን አደረገ። የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፣ ከሹማምቱና ከሕዝቡ ተወገደ፤ አንድም ዝንብ እንኳ አልቀረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴ እንደ አለ አደረገ፤ የውሻውንም ዝንብ ከፈርዖን፥ ከሹሞቹም፥ ከሕዝቡም አራቀ፤ አንድ ስንኳ አልቀረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴ እንዳለ አደረገ፤ የዝንቡንም መንጎች ከፈርዖን ከባሪያዎቹም ከህዝቡም አስነሣ፤ አንድ ስንኳ አልቀረም። |
እምቢ ብትል ግን በአንተ፥ በመኳንንትህና በሕዝብህ ቤቶች የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብጻውያን ቤቶችና የቆሙበት ምድር በዝንብ መንጋ የተሞላ ይሆናል።
ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።