አካዝያስ፥ ይሆያዳዕ ተብሎ የሚጠራውን ካህን ያገባች ይሆሼባዕ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ እርስዋም ከአካዝያስ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነውን ኢዮአስን ሊገድሉ ጥቂት ቀርቶአቸው ከነበሩት መሳፍንት መካከል በስውር ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን በቤተ መቅደስ አጠገብ በሚገኝ መኝታ ቤት ውስጥ ደበቀቻቸው፤ በዚህም ዐይነት በመደበቅ ኢዮአስን በዐታልያ እጅ ከመገደል አዳነችው፤
ዘፀአት 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐባይ ወንዝ በጓጒንቸሮች የተሞላ ስለሚሆን፥ ከዚያ እየወጡ ወደ ቤተ መንግሥትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህ፥ ወደ መኳንንትህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፥ እንዲሁም ወደ ምድጃህና ወደ ቡኾ ዕቃዎችህ ሳይቀር ይገባሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባይ በጓጕንቸሮች ይሞላል፤ ወጥተውም ወደ ቤተ መንግሥትህና ወደ መኝታ ክፍልህ፣ ወደ ዐልጋህም ወደ ሹማምቶችህና ወደ ሕዝብህ ቤቶች፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሖቃዎችህ ይገባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስማተኞችም በአስማታቸው እንዲህ አደረጉ፥ በግብጽም ምድር ላይ እንቁራሪቶችን አወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ሹሞችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ቡሃቃዎችህም፥ ወደ ምድጃዎችህም ይገባሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ባሪያዎችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ምድጆችህም፥ ወደ ቡሃቃዎችህም ይገባሉ፤ |
አካዝያስ፥ ይሆያዳዕ ተብሎ የሚጠራውን ካህን ያገባች ይሆሼባዕ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ እርስዋም ከአካዝያስ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነውን ኢዮአስን ሊገድሉ ጥቂት ቀርቶአቸው ከነበሩት መሳፍንት መካከል በስውር ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን በቤተ መቅደስ አጠገብ በሚገኝ መኝታ ቤት ውስጥ ደበቀቻቸው፤ በዚህም ዐይነት በመደበቅ ኢዮአስን በዐታልያ እጅ ከመገደል አዳነችው፤
ቤተ መንግሥትህን፥ የመኳንንትህንና የሕዝብህን ቤቶች ሁሉ የአንበጣ መንጋ ይሞላዋል፤ ይህም ሁኔታ ከቀድሞ አባቶችህ ዘመን እስከ አሁን ከታየው መከራ ሁሉ የከፋ ይሆናል።’ ” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ።
ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”