ዘፀአት 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደተባሉትም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታ፤ በግብጽ አገር ያለውም ትቢያ ሁሉ ወደ ተናካሽ ትንኝነት ተለወጠ፤ ሰዎችንና እንስሶችንም ሁሉ ሸፈነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፣ አሮን በትሩን እንደ ያዘ እጁን ሲዘረጋና የምድሩን ትቢያ ሲመታ፣ በግብጽ ምድር ያለው ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ። ሰውንም ሆነ እንስሳውን ተናካሽ ትንኝ ወረረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ አገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። |
እኔም ይህ ልጄ እኔን ያመልክ ዘንድ እንድትለቀው ነገርኩህ፤ አንተ ግን እምቢ አልክ፤ ስለዚህ አሁን የአንተን የበኲር ልጅ እገድላለሁ።’ ”
ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደው “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በበረሓ ለእኔ በዓል ለማድረግ እንዲሄዱ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይልሃል” አሉት።
እግዚአብሔር ሙሴን “የምድሩን ትቢያ በበትሩ እንዲመታ ለአሮን ንገረው፤ በግብጽም አገር ሁሉ ትቢያው ወደ ተናካሽ ትንኝነት ይለወጣል” አለው።
ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።