ምንም ገለባ ሳይሰጠን ጡብ እንድንሠራ ታዘናል፤ ከዚህም ጋር እነሆ፥ እየተገረፍን ነው፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም” ሲሉ አቤቱታቸውን አቀረቡ።
ዘፀአት 5:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም መልሶ “እናንተ ሥራ የማትወዱ ሰነፎች ናችሁ፤ በፍጹም ሰነፎች ናችሁ፤ ‘ሄደን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንድናቀርብ ልቀቀን’ እያላችሁ የምትጠይቁበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም እንዲህ አለ፤ “ልግመኞች! እናንተ ልግመኞች! እየደጋገማችሁ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔር እንሠዋ’ የምትሉት ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አላቸው፦ “ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለጌታም እንሠዋ’ ትላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን፥ “እናንተ አርፋችኋል፤ ቦዝናችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔርም እንሠዋ’ ትላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ “ሰልችታችኋል፤ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔርም እንሠዋ’ ትላላችሁ። |
ምንም ገለባ ሳይሰጠን ጡብ እንድንሠራ ታዘናል፤ ከዚህም ጋር እነሆ፥ እየተገረፍን ነው፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም” ሲሉ አቤቱታቸውን አቀረቡ።
በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ከቶ ገለባ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን ቀድሞ የምትሠሩትን ያኽል ጡብ እየሠራችሁ ማስረከብ ይኖርባችኋል!” አላቸው።
ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”