የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖሬ አላውቅም፤ ዘወትር በድንኳን ውስጥ ሆኜ ከቦታ ወደ ቦታ እዘዋወር ነበር፤
ዘፀአት 40:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉበትን ጽላት የያዘውን የቃል ኪዳኑን ታቦት በውስጡ አኑር፤ ለመከለያ የተሠራውንም መጋረጃ ከፊት ለፊቱ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምስክሩን ታቦት በውስጡ አኑር፤ ታቦቱንም በመጋረጃው ጋርደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፥ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፥ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ። |
የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ባርነት ነጻ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖሬ አላውቅም፤ ዘወትር በድንኳን ውስጥ ሆኜ ከቦታ ወደ ቦታ እዘዋወር ነበር፤
“ከግራር እንጨት የተሠራ አንድ ሣጥን፥ ታቦት አድርገው ይሥሩ፤ ርዝመቱ መቶ ዐሥር የጐኑ ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ስድሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ይሁን፤
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።
ከኰርማውም ደም ጥቂት ወስዶ በጣቱ እየነከረ በስርየት መክደኛው ላይ ከፊት ለፊት በኩል ይርጭ፤ እንዲሁም ከእርሱ ጥቂቱን በኪዳኑ ታቦት ፊት ሰባት ጊዜ ይርጨው።
“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።