የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
ዘፀአት 40:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች ወስዶ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስቀመጣቸው፤ መሎጊያዎችንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው፤ መሎጊያዎቹንም ከታቦቱ ጋራ አያያዛቸው፤ የስርየት መክደኛውንም በላዩ ላይ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ዘንድ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤ |
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ ነገር አልነበረም።
እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።
ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።
እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው።
እኔም ከተራራው ተመልሼ በመውረድ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን በሠራሁት ታቦት ውስጥ አኖርኳቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እነሆ፥ በዚያው ውስጥ ይገኛሉ።”
እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።
በዚህችኛዋ ክፍል ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት ነበሩባት፤ ከዚህችም የኪዳን ታቦት ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብ፥ ለምልማ የነበረችው የአሮን በትር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባት ጽላት ነበሩ።