ዘፀአት 39:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አሮንና ልጆቹ በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸው የተቀደሱና ውብ የሆኑ የክህነት አልባሳት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች አመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ። |
በደረት ኪሱ ላይ ያሉትን ቀለበቶች በኤፉዱ ላይ ካሉት ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ድሪ እሰራቸው፤ በዚህ ዐይነት የደረት ኪሱ ከመታጠቂያው በላይ ስለሚሆን ልል አይሆንም።
ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።
ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑት መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹና የሚቆሙባቸው እግሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ የተሠራው መጋረጃና አውታሮቹ፥ ድንኳኑ የሚተከልባቸው ካስማዎች፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ የመገልገያ ዕቃዎች፥