ዘፀአት 37:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውስጡንም ውጪውንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውስጥና በውጭ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውስጡንና ውጪውን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጥዋም፥ በውጭዋም በጥሩ ወርቅ ለበጣት፤ በዙሪያዋም የወርቅ አክሊል አደረገላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውስጥም በውጭም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አደረገለት። |
ባጽልኤልም ከግራር እንጨት የቃል ኪዳኑን ታቦት ሠራ፤ ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር።
ለመሸከሚያ የሚያገለግሉ አራት የወርቅ ቀለበቶችም አደረገለት፤ እነርሱንም በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች በሌላውም ወገን ሁለት ቀለበቶች በማድረግ በአራቱ እግሮች ላይ አኖራቸው፤