ዘፀአት 32:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም “ይህ የምሰማው የዘፈን ድምፅ እንጂ የድል አድራጊዎች ድንፋታ ወይም የተሸነፈ ሕዝብ የለቅሶ ጫጫታ አይደለም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም፣ “የድል ድምፅ አይደለም፤ የሽንፈትም ድምፅ አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ይህ የድል ነሺዎች ድምጽ ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፥ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም፥ “ይህ የድል ነሺዎች ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፤ ነገር ግን የወይን ስካር ድምፅ እሰማለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ይህ የድል ነሺዎች ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፥ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ አለው። |
ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ከቤተ መቅደሱ ተዘርፈው የመጡትን የወርቅ ዕቃዎች አስመጥተህ አንተና መኳንንቶችህ፥ ሚስቶችህና ቁባቶችህ የወይን ጠጅ መጠጫ አደረጋችኋቸው፤ ከጠጣችሁም በኋላ ማየት ወይም መስማት የማይችሉትንና ምንም ነገር የማያውቁትን ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት አመሰገናችሁ፤ መግደል ወይም ማዳን የሚችለውንና አካሄድህን የሚቈጣጠረውን ሕያው አምላክ ግን አላከበርከውም።