በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን።
ዘፀአት 30:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርዝመቱ አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር የጐኑ ስፋት አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር ከፍታውም ዘጠና ሳንቲ ሜትር ሆኖ የተስተካከለ አራት ማእዘን ይሁን። በአራቱም ማእዘን ያሉት ጒጦች ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ይሁኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዝመቱና ጐኑ ባለአንድ አንድ ክንድ የሆነ ከፍታውም ሁለት ክንድ የሆነ አራት ማእዘን ይሁን፤ ከመሠዊያው ጋራ አንድ ወጥ የሆኑ ቀንዶች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ ይሁን፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ቁመቱ ሁለት ክንድ ይሁን፤ ቀንዶቹ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ቁመቱም ሁለት ክንድ ይሆናል፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ይሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታውም ሁለት ክንድ ይሆናል፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድነት የተሠሩ ይሁኑ። |
በአራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ጠርበህ ቀንድ መሳይ ጒጦች አውጣ፤ ይህም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠራ ይሁን፤ እርሱም በነሐስ የተለበጠ ይሁን።