ዘፀአት 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም “እኔ ወደ እስራኤል ሕዝብ ሄጄ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ በምላቸው ጊዜ እነርሱ ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እመልስላቸዋለሁ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም እግዚአብሔርን፣ “ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፣ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል’ ስላቸው ‘ስሙ ማን ነው?’ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “እኔ ወደ እስራኤል ልጆች ሄጄ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ’ ባልሁ ጊዜ፦ ‘ስሙ ማን ነው?’ ቢሉኝ፥ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች እሄዳለሁ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ እላቸዋለሁ፤ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ብለው በጠየቁኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ ‘የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ’ ባልሁም ጊዜ፦ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። |
እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።
እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።
እንዲህም በለው፥ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር በበረሓ ያገለግሉት ዘንድ ሕዝቡን እንድትለቅ እንድነግርህ ወደ አንተ ልኮኛል፤ አንተ ግን እስከ ዛሬ እምቢ ብለሃል።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
የአባቶቻችን የአብርሃም፥ የይስሐቅና፥ የያዕቆብ አምላክ ልጁን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እርሱን በጲላጦስ ፊት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስም ሊለቀው ቢፈልግ እንኳ ‘አንፈልግም’ አላችሁ።
ከዚህ በኋላ ሴቲቱ መጥታ ለባልዋ እንዲህ አለችው፤ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ እኔ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤