ዘፀአት 27:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምዕራብ በኩል አደባባይ ዐሥር እግሮች ካሉአቸው ዐሥር ምሰሶዎች ጋር ርዝመታቸው ኻያ ሁለት ሜትር የሚሆን መጋረጃዎች ይኑሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ ዐምሳ ክንድ ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምዕራብ በኩል ላለው ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር እግሮች ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥርም ምሰሶዎች፥ ዐሥርም እግሮች ይሁኑለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች፥ አሥርም ምሰሶች፥ አሥርም እግሮች ይሁኑለት። |
በቅጥር ግቢው መጋረጃዎች፥ በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው የቅጥር ግቢው በር መጋረጃ፥ በአውታሮቹ፥ እንዲሁም ለእነርሱ መጠቀሚያ በሚሆኑ ዕቃዎች ሁሉ ላይ ነው።