ዘፀአት 26:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም ሥር አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ሁለቱን ተራዳዎች ለማያያዝ እንዲረዱ እያንዳንዱ ተራዳ ሁለት እግሮች ይኑሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጕጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሀያውም ሳንቃዎች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሃያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። ከሌላውም ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ። |
ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ ለእነዚህ ምሰሶዎች ከነሐስ የተሠሩ አምስት እግሮች አብጅላቸው።
ከብሩም ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚሆነው ለተቀደሰው ድንኳንና ለመጋረጃዎች መቆሚያ የሚሆኑ አንድ መቶ እግሮች የተሠሩበት ነበር፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ እግር ሠላሳ አራት ኪሎ ግራም ተመድቦለት ነው።
የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።