ዘፀአት 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለውጪው ክዳን ይሆኑ ዘንድ፥ አንደኛው ቀይ ቀለም ከተነከረ አውራ በግ ቆዳ፥ ሌላው ከተለፋ የፍየል ቆዳ ሁለት ተጨማሪ ክዳኖችን ሥራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቈዳ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአቆስጣ ቍርበት አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት አድርግ። |
በርዝመቱ በኩል ከእያንዳንዱ መጋረጃ ትርፍ ሆነው የቀሩት ግማሽ ሜትር ስፋት ያላቸው መጋረጃዎች በጐንና ጐን ተንጠልጥለው ድንኳኑን ይሸፍኑት።
ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ እንዲሁም የለፋ ቊርበት ያለው ሁሉ ይዞ መጣ።
ከውጪ በኩል መክደኛ ይሆኑ ዘንድ አንደኛውን ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፥ ሌላውንም ከለፋ ቊርበት ሌሎች ሁለት መጋረጃዎችን ሠሩ።
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።