ዘፀአት 24:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት ወስደው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡ ወጣቶች ወንዶችን ላከ፤ እነርሱም ወይፈኖችን የአንድነት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወጣት ወንድ እስራኤላውያንን ላከ፤ እነርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ወይፈኖችን የኅብረት መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለጌታም የሰላም መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤል ልጆች ወጣቶችን ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልንም ልጆች ጐልማሶች ላከ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም አቀረቡ፤ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጎበዛዝት ሰደደ። |
ከዚህም በኋላ የትሮ የሙሴ ዐማት በሙሉ የሚቃጠል ቊርባንና ሌላም ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አመጣ፤ አሮንና የእስራኤል አለቆችም ሁሉ የተቀደሰውን ምግብ በአምልኮት ሥርዓት በእግዚአብሔር ፊት ለመመገብ ከሙሴ ዐማት ጋር መጡ።
ለእኔ ከጭቃ የተሠራ መሠዊያ አብጁልኝ፤ በእርሱም ላይ ከበጎቻችሁ፥ ከፍየሎቻችሁና ከከብቶቻችሁ መርጣችሁ የሚቃጠልና የአንድነት መሥዋዕት አድርጋችሁ ሠዉበት፤ ስሜ እንዲታሰብበት በወሰንኩት ስፍራ ሁሉ ወደ እናንተ መጥቼ እባርካችኋለሁ፤