ዘፀአት 22:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው የሌላውን ሰው ገንዘብ ወይም የከበረ ዕቃ በዐደራ ለመጠበቅ ተስማምቶ ከቤቱ ተሰርቆበት ሌባው ቢገኝ እጥፍ አድርጎ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ብሩ ወይም ንብረቱ ያለ ሥጋት ይጠበቅለት ዘንድ ለጎረቤቱ ሰጥቶ ሳለ ቢሰርቅበትና፣ ሌባው ቢያዝ ዕጥፍ ይክፈል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌባው ግን ባይገኝ፥ እጁን በባልንጀራው ንብረት ላይ እንዳልዘረጋ እንዲታወቅ ባለቤቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቅረብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ዕቃ እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በባልንጀራው ዘንድ ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት አደራ ቢያኖር ከቤቱም ቢሰረቅ፥ ሌባው ቢገኝ ስለ አንድ ሁለት ይክፈል። |
“አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሌባ በሚያዝበት ጊዜ እንደሚያፍር፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝብ ነገሥታትና መኳንንት፥ ካህናትና ነቢያት ሁሉ የምታፍሩበት ጊዜ ይመጣል።
እርሱ ይህን የተናገረው፥ ለድኾች አዝኖ ሳይሆን፥ ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢት የሚይዝ እርሱ በመሆኑ በከረጢቱ የሚከተተውን ገንዘብ መውሰድ ለምዶ ነበር።