ዘፀአት 22:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እሳት ተነሥቶ ወደ ቍጥቋጦ ቢዘምትና ክምርን ወይም ያልታጨደን እህል ወይም አዝመራውን እንዳለ ቢበላ፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሳ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰው ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥ፥ ከቤቱም ቢሰረቅና ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እሳት ቢነሣ ጫካውንም ቢይዝ፥ ዐውድማውንም፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል እሳቱን ያነደደው ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ። |
“አንድ ሰው እንስሶቹ በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ ሳለ እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት ከራሱ ማሳ ወይም የወይን ተክል ቦታ ከሚያገኘው ምርት ካሣ ይክፈል።
“ስለ ከብት፥ ስለ አህያ፥ ስለ በግ ስለ ልብስና ወይም ስለ ማንኛውም የጠፋ ዕቃ ሁለት ሰዎች ቢካሰሱ፥ ስለ ንብረቱ ባለቤትነት የተጣሉት ሁለቱ ሰዎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ይቅረቡ፤ እግዚአብሔር በደሉን በዳኞቹ አማካይነት የሚገለጥበት ሰው፥ ለተበደለው ሰው ዕጥፍ አድርጎ ይክፈል።