Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “አንድ ሰው እንስሶቹ በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ ሳለ እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት ከራሱ ማሳ ወይም የወይን ተክል ቦታ ከሚያገኘው ምርት ካሣ ይክፈል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “አንድ ሰው ከብቶቹን በመስክ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ እንዲሁ ስድ ቢለቅቃቸውና የሌላውን ሰው መስክ ቢግጡ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክ ወይም የወይን ቦታ መክፈል አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “የሰ​ውን አዝ​መራ ከብ​ቱን ያስ​በላ፥ የሌላ ሰው ወይ​ን​ንም ያስ​በላ ሰው ቢኖር ግም​ቱን ይክ​ፈል። የሰ​ውን አዝ​መራ ፈጽሞ ቢያ​ስ​በላ ግን በአ​ጠ​ገቡ ባለ አዝ​መራ ልክ ይክ​ፈል፤ ወይ​ንም ቢሆን በአ​ጠ​ገቡ ባለ ወይን ልክ ይክ​ፈል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥ የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም ወይኑ ይካስ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:5
7 Referencias Cruzadas  

የድካሙን ፍሬ መልሶ ያስረክባል እንጂ አይበላም፤ ነግዶ ባተረፈውም ሀብት አይደሰትበትም።


የእንስሳውን ዋጋ ይክፈል፤ ገንዘቡን ለእንስሳው ባለቤት ከከፈለ በኋላ የሞተውን እንስሳ ለራሱ ያስቀር።


እንስሳው የተሰረቀ ከሆነ ግን ለባለቤቱ ይመለስለት፤


የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት ቢገኝ ለያንዳንዱ ዕጥፍ ዋጋ ይክፈል።


“አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል።


ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos