ዘፀአት 18:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተን ራስህንም ሆነ ሕዝቡን በከንቱ ታደክማለህ፤ ብቻህን ሆነህ ይህን ሁሉ ለመሥራት ይከብድብሃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተና ወደ አንተ የሚመጡት እነዚህ ሰዎች የምታደርጉት ነገር ቢኖር ራሳችሁን ማድከም ነው፤ ሥራው ለአንተ ከባድ ሸክም ነው፤ ብቻህን ልትወጣው አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድሃልና፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ፥ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድብሃል፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። |
ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?
እናንተ በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን ርዳታ እርሱ ለማሟላት ብሎ ስለ ክርስቶስ ሥራ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሞት ተቃርቦ ነበር።