ዘፀአት 16:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር፥ በዐሥራ አምስተኛው ቀን፥ ከኤሊም ተነሥተው በሲና እና በኤሊም መካከል ወዳለው “ሲን” ተብሎ ወደሚጠራው ምድረ በዳ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኤሊምም ተነሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር፥ በዓሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከኤሎም ተጓዙ፤ ከግብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በኤሎምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤሊምም ተጓዙ፥ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከግብፅ አገር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። |
መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።