እንግዲህ ለሰው የሚጠቅመው ነገር ቢኖር፥ ደክሞ በመሥራት ያፈራውን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት ራሱን ለማስደሰት መቻሉ ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ተረድቼአለሁ።
መክብብ 2:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ እርሱ ፈቃድማ እየበላና እየጠጣ ተድላ ደስታ ማድረግ የሚችል ማን አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ዘንድ ካልሆነ ማን መብላትና መደሰት ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ እርሱ ፈቃድ ማን ይበላል፥ ማንስ ተድላን ይቀምሳል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ እርሱ ፈቃድ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማን ነው? |
እንግዲህ ለሰው የሚጠቅመው ነገር ቢኖር፥ ደክሞ በመሥራት ያፈራውን ሁሉ በመብላትና በመጠጣት ራሱን ለማስደሰት መቻሉ ነው፤ ይህም ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን ተረድቼአለሁ።
እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።