መክብብ 12:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! ልትጠነቀቅባቸው የሚገባ ሌሎች ነገሮች አሉ፤ መጻሕፍትን ጽፎ ለመጨረስ ከቶ አይቻልም፤ የምርምርም ብዛት ሰውነትን ያደክማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ በማንኛውም ነገር ተጠንቀቅ፤ አንዳችም አትጨምር። ብዙ መጻሕፍትን መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፥ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፥ ፍጻሜ የሌላቸው ብዙ መጻሕፍትን አታድርግ። እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ስማ፥ ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል። |
ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ እርሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ቢጻፉ ኖሮ የሚጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ራሱ መሸከም ባልቻለም ነበር።