መክብብ 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨዋነት ያደገ ንጉሥና ለስካር ሳይሆን ብርታትና ኀይል ለማግኘት ብቻ በተወሰነ ጊዜ የሚበሉና የሚጠጡ መሪዎች ያሉአት አገር የተባረከች ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ ንጉሥሽ ከተከበረው ዘር የሆነ፣ ለመስከር ሳይሆን ለብርታት፣ በተገቢው ጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ ምድር ሆይ፤ ብፁዕ ነሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥሽ የጌታ ልጅ የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ለብርታት በጊዜ የሚበሉ፥ የማያፍሩም፥ አንቺ ሀገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሥሽ የከበረ ልጅ የሆነ፥ ለብርታት እንጂ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ የተመሰገንሽ ነሽ። |
የራሳቸው ወገን ከመካከላቸው ተነሥቶ መሪአቸው ይሆናል፤ እኔ ራሴ ስለማመጣው እርሱ ወደ እኔ ይቀርባል፤ አለበለዚያማ ማን ደፍሮ ሊቀርብ ይችላል?
እዚያም በገንዘቡ የምተፈልገውን ነገር ከብት፥ ወይም በግ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ጠንካራ መጠጥ፥ ወይም ማንኛውንም የመረጥከውን ነገር ገዝተህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አንተና ቤተሰብህ በመብላት ተደሰቱ።