መክብብ 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጥበብንና ዕውቀትን፥ እብደትንና ሞኝነትን ዐውቅ ዘንድ ኅሊናዬን አተጋለሁ፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ሆኖ አገኘሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የጥበብንና የእብደትን፣ የሞኝነትንም ነገር ለመገንዘብ ራሴን አተጋሁ፤ ይህም ነፋስን እንደ መከተል መሆኑን ተረዳሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብንና ዕብደትን ሞኝነትንም አውቅ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ ይህም ደግሞ ነፋስን መከተል እንደሆነ አስተዋልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤም ብዙ ጥበብንና አእምሮን፥ ምሳሌንና ማስተዋልን ተመለከተች። ይህም ነፋስን መከተል እንደ ሆነ አስተዋልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥበብንና ዕብደትን ሞኝነትንም አውቅ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ ይህም ደግሞ ነፋስን እንደ መከተል እንደ ሆነ አስተዋልሁ። |
ከመከራ በቀር ያገኘሁባት ጥቅም ባለመኖሩ ሕይወት በእኔ ዘንድ ትርጒም አልተገኘላትም፤ ይህም ከንቱ ስለ ነበር ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ይቈጠራል።
ይህም ሁሉ ሆኖ ጥበብን ለማግኘት ባለኝ ምኞት በመመራት ልቤን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ የምዝናናበት ጊዜ እንዲኖረኝ ለማድረግ በሞኝነት ወሰንኩ፤ ሰዎች ሁሉ በምድር ላይ በሚኖሩበት በአጭር ዕድሜአቸው ሊያገኙት የሚገባ የተሻለ መልካም ዕድል ይህ ብቻ መሆኑን አሰብኩ።
በእርግጥም የሰው ልጆችና የእንስሶች ዕድል ፈንታቸው አንድ ዐይነት ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁለቱም የተፈጥሮ እስትንፋስ አንድ ዐይነት ነው፤ ታዲያ ሁለቱም ከንቱ ስለ ሆኑ ሰው ከእንስሳ አይሻልም።
ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።
የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።